Baga Ayyaana Irreechaa bara 2018 nagaan geessan!
Irreechi Obbolummaadhaaf!
"ለወንድማማችነት!" - የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ የእሬቻ በዓልን በድምቀት አከበረ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ፣ "የዘንድሮ እሬቻ ለወንድማማችነት!" በሚል መሪ ቃል የእሬቻ በዓልን በስሩ ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር በመተባበር በደማቅ ስነ-ስርዓት አከበረ። በዓሉ የወንድማማችነትን፣ የአንድነትንና የምስጋናን እሴቶች በሚያንፀባርቁ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ታጅቦ ተከብሯል።
የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ማህበረሰብ አባላት የኦሮሞን ባህልና የእሬቻን እሴቶች በሚያንጸባርቁ ያማሩ ባህላዊ አልባሳት አሸብርቀው በዓሉን አድምቀዋል ።
የዘንድሮው መሪ ቃልም የበዓሉን ትስስርና አብሮነት ይበልጥ አጉልቶታል።
በዓሉ የኦሮሞ ማህበረሰብ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሸጋገሩን የሚያበስርበት ከመሆኑም ባሻገር፣ እንደ ሀገር ለወንድማማችነትና ለአብሮነት መጠናከር ያለውን ጉልህ ሚና የሚያሳይ ነው።
የእሬቻ በዓል በኢትዮጵያ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ በድምቀት የሚከበርና በዩኔስኮ በማይዳሰሱ የዓለም ቅርሶች መዝገብ ላይ እንዲሰፍር ጥረት እየተደረገለት የሚገኝ ታላቅ የባህልና የምስጋና በዓል ነው።


.