ማክሰኞ ሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
________________________________________
በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ተቋማዊ የሙያ ብቃት ምዘና ተጀመረ
________________________________________
ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ
የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2017 ዓ.ም የማርኬቲንግ ዲፓርትመንት የማታ ተመራቂ ሰልጣኞችን የሙያ ብቃት ለመመዘን ተቋማዊ የሞዴል ምዘና መስጠት ጀመረ።
ሰልጣኞቹ ይህንን ተቋማዊ የሞዴል ምዘና በማጠናቀቅ፣ የሙያ ብቃት ምዘና ማዕከል ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ዝግጅት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
በኮሌጁ እየተሰጠ ያለው ምዘና የፅንሰ ሀሳብ ሲሆን፣ በጽሁፍ እየተሰጠ ይገኛል።
በኮሌጁ የስልጠና እና አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን የሆኑት አቶ እንድሪስ መሐመድ እንደገለጹት፣ የተቋማዊ ምዘናው ዋና ዓላማ ሰልጣኞች ለሀገር አቀፉ የብቃት ምዘና ከመቅረባቸው በፊት ያላቸውን እውቀትና ክህሎት ለመፈተሽ እንዲሁም ያለባቸውን ክፍተት ለመሙላት ነው።
የ2017 የማታ ተመራቂ ሰልጣኞች ነሐሴ 25 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚመረቁ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ሰልጣኞች መመረቅ የሚችሉት የሙያ ብቃታቸውን ሲያረጋግጡ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።



.