Announcement ✨ ወርቃማ ሰኞ ✨ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ

✨ ወርቃማ ሰኞ ✨ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ

14th October, 2025

✨ ወርቃማ ሰኞ ✨

የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ

በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ሳምንታዊ የ'ወርቃማ ሰኞ' መድረክ ላይ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥን ጥራት በማሳደግ የህዝብ እርካታን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥልጠና ተካሄደ። ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ መድረክ ላይ፣ በኮሌጁ የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት ባልደረባ በአቶ አማረ ንጉስ አማካኝነት ዝርዝር የሥልጠና ጽሑፍ ቀርቧል።

የአገልግሎት አሰጣጣቸውን በማዘመን ለሀገራዊ ልማትና መልካም አስተዳደር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማገዝን ዓላማ ያደረገ መሆኑን አቶ አማረ ገልጸዋል። እርሳቸው እንዳብራሩት፣ አገልግሎት በእውቀትና በሙያ ላይ ተመስርቶ የደንበኞችን ፍላጎት የማሟላት ጥረት ሲሆን፣ የማይዳሰስ፣ ከአገልግሎት ሰጪው የማይለይና የማይከማች መሆኑ የአገልግሎት ጥራትን ለመጠበቅ የሰራተኛውን ሥነ-ምግባር ወሳኝ ያደርገዋል።

ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠትም ተቋማት በውስጥና በውጭ ደንበኞች መካከል ያለውን ልዩነት ተገንዝበው፣ የደንበኛ ተኮር የአሰራር መርሆዎችን መከተል እንደሚገባቸው ተጠቁሟል።

የደንበኞች ቅሬታ እንደ የአገልግሎት ማሻሻያ ግብዓት መቆጠር እንዳለበት የተገለጸ ሲሆን፣ ለሚነሱ ቅሬታዎች ፈጣንና ፍትሐዊ ምላሽ መስጠት የተቋማትን ተአማኒነት እንደሚያሳድግ ተገልጿል።

ለሰጡት አነቃቂ የዕውቀት ሽግግር በአቶ አማረ ንጉስን ከልብ እናመሰግናለን!

.

Copyright © All rights reserved.

Created with