እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!
የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ በስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና አፈጻጸም ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ
የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በ2017 በጀት ዓመት ባካሄደው ግምገማ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብና በኮሌጆች ዘርፍ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የዋንጫና የሰርተፍኬት አሸናፊ ሆኗል።
ይህ ሽልማት ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ የስነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች በሰጠው የእውቅና መርሃግብር ላይ የተበረከተ ነው። የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ያስመዘገበው ይህ ውጤት፣ በተቋሙ ውስጥ የሙስና መከላከልና የስነ ምግባር ግንባታ ስራዎች የደረሱበትን ከፍተኛ ደረጃ የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
የኮሌጁ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ባህሩ ምኑየለት፣ ይህ ድል የመላው የኮሌጁ ማህበረሰብ የጋራ ጥረት ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ ድል የሁላችንም ነው
ያሉት አቶ ባህሩ፣
ለዚህ ስኬት የኮሌጁ አመራሮች፣ አሰልጣኞች፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና ሰልጣኞች ላደረጉት የተቀናጀ አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋና ይገባቸዋል
በማለት የስኬቱ ባለቤቶች ሁሉም መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ይህ እውቅና የኮሌጁን የፀረ-ሙስና ትግል ቁርጠኝነት እና ስኬታማነት በግልጽ የሚያረጋግጥ ከመሆኑም በላይ፣ በቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች ትልቅ መነቃቃትን እንደሚፈጥር ተገልጿል።
እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ!


.