Announcement በ" አራተኛ ሳምንት ወርቃማ ሰኞመድረክ" Emotional Intelligence የስሜታዊ ብልህነት

በ" አራተኛ ሳምንት ወርቃማ ሰኞመድረክ" Emotional Intelligence የስሜታዊ ብልህነት

02nd September, 2025

ወርቃማ ሰኞ

ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ

በ"ወርቃማ ሰኞ" መድረክ

Emotional Intelligence የስሜታዊ ብልህነት በአቶ ፋንታሁን አበበ

ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ፣ በየሳምንቱ ሰኞ በሚያዘጋጀው "ወርቃማ ሰኞ" መድረክ ላይ የስሜታዊ ብልህነት (Emotional Intelligence) በግልና በሙያዊ ህይወት ስኬት ላይ ያለውን ወሳኝ ሚና ያተኮረ ገለጻ ። 

በኮሌጁ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ መድረክ ላይ የኮሌጁ አሰልጣኞች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል። አቶ ፋንታሁን አበበ በሰጡት ጥልቅ ገለጻ፣ የስሜታዊ ብልህነት ምንነት፣ ራስንና የሌሎችን ስሜት የመረዳት አስፈላጊነት፣ በግልና በቡድን ስራ ላይ የሚያመጣው በጎ ተጽዕኖ እንዲሁም ክህሎቱን ለማዳበር የሚረዱ ተግባራዊ መንገዶችን በስፋት አብራርተዋል።

አቶ ፋንታሁን በስልጠናው ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ 

ስሜትን መረዳት፣ መቆጣጠር እና የሌሎችን ስሜት በመገንዘብ ግንኙነትን ማሻሻል በ21ኛው ክፍለ ዘመን ለስኬት ወሳኝ ክህሎት ነው" ብለዋል። አክለውም፣ "በተለይ እንደ ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ባሉ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ፣ ከማሽን ጋር ብቻ ሳይሆን ከሰዎች ጋር በብቃት መስራት ይጠበቅባችኋል፤ ይህም የስሜታዊ ብልህነትን አስፈላጊነት ከፍ ያደርገዋል

ሲሉ አስገንዝበዋል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with