ማክሰኞ ፡- ሰኔ 23 ፣2017 ዓ.ም
ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የአሰልጣኞችና የአስተዳደር ሰራተኞች ISO 21001:2018ን በተመለከተ በኦዲት ስራዎች ዙሪያ የሁለት ቀናት ስልጠና ወሰዱ። ስልጠናው ሰኔ 23 እና 24 ቀን 2017 ዓ.ም. የተካሄደ ሲሆን፣ በአቶ ታደሰ ተስፋዬ አማካኝነት ተሰጥቶአል፤ በዓለም አቀፉ የትምህርት ድርጅቶች ማኔጅመንት ሲስተም (EOMS) ደረጃዎች መሰረት የውስጥ ኦዲት ክህሎቶችን ለማዳበር ያለመ ነበር።
በዚህ ስልጠና ላይ ተሳታፊዎች ስለ ISO 21001:2018 መሰረታዊ መርሆች፣ መስፈርቶች እና እንዴት የትምህርት ጥራት ማኔጅመንት ስርዓትን መገንባትና ማስኬድ እንደሚቻል ጥልቅ ግንዛቤ አግኝተዋል። በተለይም የኦዲት ስራዎችን በሚመለከት፣ የኦዲት እቅድ ማውጣት፣ መረጃ መሰብሰብ፣ ግኝቶችን መተንተን እና ሪፖርት ማቅረብ በሚሉ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ልምምድ ተደርጓል። ይህም ኮሌጁ የጥራት ደረጃውን የጠበቀ የውስጥ ኦዲት ስርዓት እንዲዘረጋና እንዲያጠናክር ያስችለዋል።
ስልጠናው በኮሌጁ የአካዳሚክ እና የአስተዳደር ሂደቶች ውስጥ የጥራት ደረጃዎችን ለማስጠበቅ የሚደረገውን ጥረት የሚያጠናክር ሲሆን፣ የአሰልጣኞችንና የአስተዳደር ሰራተኞችን ብቃት በማሳደግ የተሻለ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።



.