Announcement በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት አከባበር ላይ ውይይት ተካሄደ

በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት አከባበር ላይ ውይይት ተካሄደ

25th September, 2025

በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት አከባበር ላይ ውይይት ተካሄደ

መስከረም 14፣ 2018 ዓ.ም.

በልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት አከባበርን አስመልክቶ ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ በዓላቱ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው መከበር እንዳለባቸው ተገለጸ።

የውይይት ሰነዱን ያቀረቡት የቴክኖሎጂ ልማትና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ምክትል ዲን የሆኑት ወ/ሮ የሺወርቅ እንየው፣ እነዚህ ታላላቅ የአደባባይ በዓላት የኢትዮጵያ የብዝሃነት መገለጫና የህዝብን አንድነት የሚያጠናክሩ እንደመሆናቸው፣ ዋና ማንነታቸውን ሳይለቁ መከበር አለባቸው ብለዋል።

"የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ለዘመናት የቆዩ፣ በውስጣቸው ሰፊ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቶችን የያዙ ናቸው" ያሉት ወ/ሮ የሺወርቅ፣ "እኛ የዚህ ትውልድ ባለአደራዎች እንደመሆናችን እነዚህን እሴቶች ሳንሸረሽር ለቀጣዩ ትውልድ የማስረከብ ታሪካዊ ኃላፊነት አለብን" ሲሉ በኮሌጁ ለተገኙ ተሳታፊዎች አሳስበዋል።

በዓላቱ ለቱሪዝም መስህብነት ያላቸውን ጠቀሜታ የጠቀሱት ምክትል ዲኗ፣ ይህንንም ተከትሎ የሚመጡ የውጭ ጎብኚዎች የኢትዮጵያን ትክክለኛ ገጽታ የሚረዱት በዓላቱ በባህላዊና ሃይማኖታዊ ይዘታቸው ሲከበሩ መሆኑን አስምረውበታል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የኮሌጁ ማህበረሰብ አባላት በበኩላቸው፣ የቀረበውን ሀሳብ በመደገፍ "እነዚህን የአደባባይ ላይ በዓላት ስናከብር ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻችን ተጠብቀው ለትውልድ መተላለፍ በሚችሉበት አግባብ መሆን ይገባዋል" ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በመጨረሻም በመድረኩ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በኮሌጁ ዲኖች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።


.

Copyright © All rights reserved.

Created with