Announcement ✨ ወርቃማ ሰኞ ✨ የህዳሴ ግድባችን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት ነው

✨ ወርቃማ ሰኞ ✨ የህዳሴ ግድባችን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት ነው

25th September, 2025

የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን በታላቅ ድምቀት አከበረ

መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም.

የልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ማህበረሰብ የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅና ስራ መጀመርን 

የህዳሴ ግድባችን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት ነው

በሚል መሪ ቃል በታላቅ ድምቀት አክብሯል።

በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ፅ/ቤት የተዘጋጀው 

በህብረት ችለናል

የተሰኘ የመወያያ ሰነድ መነሻነት በተካሄደው ውይይት፣ የኮሌጁ ምክትል ዲን ወ/ሮ ትዕግስት ድንቁ ዋና አቅራቢ ሆነው አገልግለዋል።

በውይይቱ ላይ የኮሌጁ ማህበረሰብ፣ የአባይ ግድብ መገንባት ለኢትዮጵያዊያን የጋራ መግባባትና ድል ምልክት መሆኑን በማረጋገጥ፣ 

የአባይ ግድብ ብሄራዊ ኩራታችን ዳግማዊ አድዋ

ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የኮሌጁ አሰልጣኞች እና የአስተዳደር ሰራተኞች በግድቡ ግንባታ ወቅት ያደረጉትን አስተዋፅኦ በመግለጽ። ከዚህም በተጨማሪ፣ በመጪው ጊዜም መንግስት ለሚያካሂዳቸው ማንኛውም ፕሮጀክቶች በሙያም ሆነ በገንዘብ አስተዋፅኦ ለማድረግ ያላቸውን ጠንካራ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ይህ ክብረ በዓል፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ በጋራ ተነሳሽነትና በህዝብ ተሳትፎ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ እንደሚቻል ማሳያ ነው በማለት፣ 

በህብረት ችለናል

 የሚለው መሪ ቃል በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ የሰረፀ የመተባበር መንፈስ መሆኑን አስመስክሯል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with